ቤተ ክርስቲያናችን ሳምንታዊ የኪዳን ጸሎት፣ የሰርክ ጉባዔና የቅዳሴ አገልግሎት ይሰጣል። እንዲሁም በየወሩ ወር በገባ በ፩ኛው ቀን የቅዱስ ራጉኤልን በዓል፤ በ፲፱ኛው ቀን የቅዱስ ገብርኤልን በዓል እንዲሁም በ፳፩ኛው ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን በዓል በማሰብ ቅዳሴ ይቀደሳል። እነዚህን ሳምንታዊና ወርሃዊ የአገልግሎት መርሐ ግብሮቻችንን ለመመልከት ከዚህ በታች የቀረበውን ሰሌዳ ይመልከቱ።
ቀን
|
ሰዓት
|
መርሐ ግብር
|
እሑድ
|
4AM – 11AM
|
ጸሎተ ቅዳሴና ትምህርተ ወንጌል
|
እሑድ
|
12PM – 2PM
|
የሰንበት ት/ቤት መርሐ ግብር
|
አርብ
|
6PM – 8PM
|
የሠርክ ጸሎትና ትምህርተ ወንጌል
|
ሰኞ - ቅዳሜ
|
7AM – 10AM
|
ጸሎተ ኪዳንና መንፈሳዊ የምክር አገልግሎት
|