በመምህር ዮሐንስ ለማ የተዘጋጀ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ። 

genaሚካኤል ሊቀ መላእክት ሰአል በእንቲአነ ወቅዱስ ገብርኤል አእርግ ጸሎተነ ።

፬ቱ እንስሳ መንፈሳውያን ሰባሕያን ወመዘምራን ሰአሉ በእንቲአነ ፳ወ፬ቱ ካህናተ ሰማይኒ አዕርጉ ጸሎተነ ።

ነቢያት ወሃዋርያት ጻድቃን ወሰማዕት ሰአሉ በእንቲአነ ምስሌክሙ ከመ ይክፍለነ መክፈልተ ወርስተ ለኩልነ ።

ማሕበረ ቅዱሳን ወሰማዕት ሰአሉ በእንቲአነ መላእክተ ሰማይኒ አዕርጉ ጸሎተነ ።

ማርያም እግዝእትነ ወላዲተ አምላክ ሰአሊ በእንቲአነ እስም ረከብኪ ሞገሰ በሃበ እግዚአብሔር ።

ረከብኪ ሞገሰ መንፈሰ ቅዱሰ ወኃይለ ሰአሊ አስተምህሪ ለነ ማርያም ወልድኪ ሳህሎ ይክፍለነ ።

ኀበ ተርህወ ገነት ወሃበ ተነጽፈ እረፍት ይክፍለነ ነሃሉ ውስተ በአቶሙ ለቅዱሳን (ሦስት ጊዜ በአራራይ በል) ።

እዚሕ ጋር አቡነ ዘበሰማያት ይደገምና ስምዓኒ ይመራል ።

 

ወወሀብኮሙ  ተእምርተ ለእለ ይፈርሑከ ከመ ያምስጡ እምገጸ ቅስት ወይድኅኑ ፍቁራኒከ ፣ ከቀስት  ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ  ምልክትን ሰጠሀችው ወዳጆችህ እንዲድኑ . .

( መዝ . 59 ፥ 4 -5 )

ከመምህር ዮሐንስ  ለማ

 meskel demeraየተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንኳን ለ2ዐዐ5  ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ  የመስቀል  በዓል በሰላምና  በጤና  ሑላችንንም  አደረሰን  አደረሳችሁ ፡፡  ስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ዕለት ። ከዚህ ዘመን ፤ ከዚህ ዕለትና ከዚሕ ሰዓት ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ።   ፈጣሪያችን ቸሩ መድኅኔ ዓለም በዓሉን  የሰላም፤ የዕድገት የጤናና የበልጽግና  በዓል  ያድርግልን ለሐገራችን ለቤተክርስቲያናችን እንዲሑም ለመላው ዓለም እውነተኛውን ሰላም ፣ ፍቅር ፣ አንድነት ፣ ኅይልንና ብርታትን ይስጠን  ። ከብርሐነ መስቀሉም   ረድዔት በረከት  ያሳትፈን ።

st.gabriel-selestudkikከሁሉ አስቀድሞ በልዑል እግዚአብሔር ስም የእግዚአብሔር ሰላም፣ ጸጋ፣ በረከት፣ ፍቅርና አንድነት እንዲበዛላችሁ ዘወትር እየተመኘን በደብራችን በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ወገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤልን ዓመታዊ በዓል ታኅሳስ ፳ እና ፳፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.(December 29/30 2012) በደመቀ መንፈሳዊ ሥርዓት በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙ የየአድባራቱ ካህናት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት አባላት፣ ማኅበረ ምዕመናንና ምዕመናት በተገኙበት ከዋዜማው ጀምሮ የምናከብር መሆኑን በደስታ እየገለጽን እርስዎም የበዓሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማክበር ጠርተንዎታል።

 

የበዓል አከባበሩን መርሐ ግብር ለመመልከት እዚህ ይጫኑ። 

ከዋዜማው ጀምሮ ያለውን ሥርዓተ ማኅሌት በጽሑፍ ለመመልከትና በዜማ ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ