አባታችን ሆይ

Our Father

አባታችን ሆይ!

በሰማይ የምትኖር፥ ስምህ ይቀደስ፥ መንግሥትህ ትምጣ፥

ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ እንዲሁም በምድር ይሁን!

የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ፥ በደላችንን ይቅር በለን፥

እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል፥ አቤቱ ወደ ፈተና

አታግባን፥ ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ፥ መንግሥት ያንተ ናትና።

ኃይል፥ ክብር፥ ምስጋና ለዘለዓለም።

Our father who art in heaven, hallowed by Thy name, Thy kingdom come, Thy will be done on earth as it is in heaven; give us this day our daily bread, and forgive us our trespasses as we forgive those who trespass against us, and lead us not into temptation but deliver us from the evil one; for Thine is the kingdom, the power and the glory forever and ever.

እመቤቴ ማርያም ሆይ

Hail Mary

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ!

በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን።

በሃሳብሽ ድንግል ነሽ። በሥጋሽም ድንግል ነሽ። የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል። ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነዉ።  ጸጋን የተመላሽ ሆይ! ደስ ይበልሽ፣ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነዉና። ከተወደደዉ ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኝልን ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ።

O Our Lady, Virgin Saint Mary! In Saint Gabriel’s greetings, peace be unto you.  Holy and pure, O mother of the almighty God! Peace be unto you.  Blessed are thou amongst women and blessed is the fruit of thy womb.  Hail Mary, full of grace, the Lord is with Thee.  Pray for us before our Lord Jesus Christ that he may forgive us our sins.

የሃይማኖት ጸሎት

The Prayer of Faith (Creed)

ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን፥ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ፥

የሚታየዉንና የማይታየዉን ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋራ በነበረ አንድ የአብ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን፥

ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፥ ከእዉነተኛ አምላክ የተገኘ እዉነተኛ አምላክ፥ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ፥ በባሕርዩ ከአብ ጋር የሚተካከል፥

ሁሉ በእርሱ የሆነ፥ በሰማይም ካለዉ፥ በምድርም ካለዉ፥ ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የለም፥

እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ፥ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰዉ ሆነ፥ በጰንጤናዊዉ በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ፥ ሞተ፥ ተቀበረ፥ በሦስተኛዉም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈዉ፥ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፥ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ፥ ዳግመኛም በምስጋና ይመጣል በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ፥ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለዉም።

በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን፥ እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ፥ ከአብ የሠረጸ ከአብና ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን፥ እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረ ነዉ።

ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሩዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን።

ኃጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀትም እናምናለን።

የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን፥ የሚመጣዉንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን።

We believe in one God the Father almighty, maker of heaven, earth and all things visible and invisible.

And we believe in one Lord Jesus Christ, the only-begotten Son of the Father who was with Him before the creation of the world:

Light from light, true God from true God, begotten not made, of one essence with the father:

By whom all things were made, and without Him was not anything in heaven or earth made:

Who for us men and for our salvation came down from heaven, was made man and was incarnate from the Holy Spirit and from the Holy Virgin Mary.

Became man,  was crucified for our sakes in the days of Pontius Pilate, suffered, died, was buried and rose from the dead on the third day as was written in the holy scriptures:

Ascended in glory into heaven, sat at the right hand of His Father, and will come again in glory to judge the living and the dead; there is no end of his reign.

And we believe in the Holy Spirit, the life-giving God, who proceedeth from the Father; we worship and glorify Him with the Father and the Son; who spoke by the prophets;

And we believe in one holy, universal, apostolic church,

And we believe in one baptism for the remission of sins, and wait for the resurrection from the dead, and the life to come, world without end. Amen.

 

 

 

ሀገር

 

 

ሁለት

 

 

ሂሳብ