“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ”
“ምስጋና ለእግዚአብሔር በሰማያት ሰላምም በምድር ለሰው ልጆች ሁሉ ይሁን”
ሉቃ ፪÷፲፬

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለ2005 ዓመት የልደት በዓል በሰላምና በጤና ሁላችንንም አደረሰን አደረሳችሁ ፡፡ ስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ዕለት ። ከዚህ ዘመን ፤ ከዚህ ዕለትና ከዚህ ሰዓት ያደረሰን ልዑለ ባህርይ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ። ፈጣሪያችን ቸሩ መድኃኔ ዓለም በዓሉን የሰላም ፤ የዕድገት ፤ የጤናና የብልጽግና በዓል ያድርግልን ። ለሀገራችን ለቤተክርስቲያናችን እንዲሁም ለመላው ዓለም እውነተኛውን ሰላም ፣ ፍቅር ፣ አንድነት ፣ ኃይልንና ብርታትን ይስጠን ። ከብርሃነ ልደቱም ረድኤት በረከት ያሳትፈን።

በዓለ ልደት ሃይማኖታዊ ብሔራዊና ዓለም ዓቀፋዊ መሠረትና ገጽታ ካላቸው በዓላት አንዱና ዋነኛው በዓል ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አምላካዊ ወመጽሐፋዊ ትውፊትን መሠረት በማድረግ በየዓመቱ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት በታላቅ ዝማሬ፣ በማኅሌት፣ በቅዳሴ ... "ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ - የዓለም ሁሉ ቤዛ ዛሬ ተወለደ " እያለች የቤዛነቱን ምስጢር እየመሰከረች ፣ እያስተማረችና እያራቀቀች በታላቅ መንፈሳዊ ትሩፋትና ኢትዮጵያዊ ዘይቤ በየዓመቱ በደመቀ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት በማክበር ላይ ትገኛለች፡፡

የመልእክቱን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

ትግሁ ወቁሙ በሃይማኖት ተአገሡ ወአጥብ

 ትጉ በሃይማኖት ጽኑጨክናችሁ መከራን ታገሡ፡፡

ሮሜ 16፡13

abagebreweldአክለ ወንጌል የተዘራባችሁ፡

በዝናመ ሃይማኖት የመለማሁ፡

ፍሬ ሃይማኖት ምግባረ ጽድቅን ያፈራችሁ፡

ይህን ትምህርተ ሕይወት በመስማት ላይ ያላችሁ

ቡሩካን  ምእመናነ ክርስቶስ ሁላችሁ::

በአዕይንተ አእምሮ  በጥልቅ ሲመለከት የክርስትና ሃይማኖት የመከራ ሥጋና የመከራ ነፍስ ገዳም ነው ለማለት ይቻላል።

በገዳም የሚኖረውም ዕጽፍ ድርብ ዋጋ በሚያሰጥ ገድል ነው።

ያለ ገድል ክርስትና ያጸድቅ ዘንድ በግብር አይገለጥም። የዚህንም እውነትነት በብርሃነ ሕይወት መንፈስ ቅዱስ ተቃኝታችሁ በውል እንደምትረዱት እምነቱ የጸና ነው።