ፕሮጀክቱ ስያሜ፡

  • እምነት ተስፋ ፍቅር

የፕሮጀክቱ ርዕይ፡ 

  • በእምነት የጸኑ በፍቅር የታነጹ በሥነ ምግባር ያጌጡ ማንነታቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ለመረከብ ተስፋ ያላቸው ሕጻናት ሲኖሩ ማየት

በፕሮጀክቱ መክፈቻ መርሐ ግብር (Open House) ላይ የቀረበውን ማብራሪይ (presentation) ከዚህ በታች ይመልከቱ

Loading...

 

 በእለቱ ተዘጋጅተው ለወላጆች ከቀረቡ የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ውጤቶች መካክል፡

EmnetTesfaF...
EmnetTesfaFikirOpenHouse EmnetTesfaFikirOpenHouse
EmnetTesfaF...
EmnetTesfaFikirOpenHouse EmnetTesfaFikirOpenHouse
EmnetTesfaF...
EmnetTesfaFikirOpenHouse EmnetTesfaFikirOpenHouse
EmnetTesfaF...
EmnetTesfaFikirOpenHouse EmnetTesfaFikirOpenHouse

“ጽዮን ማርያም ሰንበት ት/ቤት” በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን  ውስጥ የሚገኝ ሲሆን  መስከረም 6፣ 2004 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤት ደረጃ የተቋቋመበትን 1ኛ ዓመት ያከብራል።    በሰንበት ት/ቤት ደረጃ ከመቋቋሙ በፊት፣ ማኅበረ ጽዮን ማርያም በመባል ይጠራ ነበር። “ጽዮን ማርያም” የሚለውም ስያሜ ከዚያ የተወሰደ ነው።

  የማኅበረ ጽዮን ማርያም አመሠራረት

          ማኅበሩ በሁለት ወንድሞች ተጠንስሶ ከሳቴ ብርሃን ጉባኤ በሄዱ ስድስት ወንድሞች ነሐሴ 30 1997 ዓ.ም ተመሠረተ። በጊዜው ማኅበሩን ለመመሥረት ያስገደዱ ሁለት ዋና ምክንያቶች  በአካባቢያችን (በዳላስ አውሮፕላን ማረፊያ) ምንም አይነት መንፈሣዊ እንቅስቃሴ አለመኖሩና በአካባቢው እየተስፋፋና እያደገ የመጣው የመናፍቃን እንቅስቃሴ ሲሆን በዕለቱ TC Williams  በሚገኘው የመኪና ማቆሚያ ላይ 3 ሰዓት የፈጀ ውይይት ተደርጎ ለማኀበሩ ስያሜ በማውጣት እና የአገልግሎት ክፍሎችን በማቋቋም ተጠናቋል። በወቅቱ ረዥም ሰዓት የፈጀው ለማኀበሩ ስያሜ መስጠት ሲሆን 5  አማራጮች ቀርበው ከቀረቡት መካከል ምንም እንኳን ሁላችንም የተለያዩ ቅዱሰንን ብንወድም ሁላችንንም የሚያስማማን የእመቤታችን ስያሜ በመሆኑ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  በስደት ለምንኖር አምባችን መጠጊያችን ስለሆነች ማኀበረ ጽዮን ማርያም በሚለው ጸንቷል።