Holy Trinity2ሐዋርያዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ክርስቲያናዊ ትውፊታዋንና ኀይማኖታዊ አስተምህሮዋን ጠብቃ የኖረች ናት ። ከአስተምህሮዋም አንዱና ዋንኛው ምሥጢረ ሥላሴ ነው ። ምሥጢረ ሥላሴ ( የእግዚአብሔር ባሕርይ ) ምሉዕና ስፉሕ ረቂቅና ምጡቅ የሆነ ተመጣጣኝ ምሳሌ የማይገኝለት ቢሆንም ፣ ቅዱሳን ነቢያትና ቅዱሳን ሐዋርያት በመንፈሰ እግዚአብሔር እየተመሩ የጻፏቸውን መጻሕፍተ ብሉያትንና መጻሕፍተ ሐዲሳትን ምስክር በማድረግ አበው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደ አስተማሩን ፣ (በምሳሌ ዘየሐጽጽ) ደካማው አዕምሯችን በሚረዳው ዕኛ በምናውቀው ለሥላሴ ተመጣጣኝ ባልሆነ በአነስተኛ ምሳሌ እየመሰልን የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት በዕርሱ አጋዥነትና ረዳትነት ለመጻፍ እጀምራለሑ ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ

ከመ/ር ዮሐንስ ለማ

የደብሩ ስብከተ ወንጌል ኅላፊ

holy trinityየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረ፤ ያለና የሚኖር አንድ አምላክ መኖሩን ታምናለች፡፡ ይኸውም አንድ አምላክ፤ በአካል፤ በስም፣ በግብር ሦስት፤ በመለኮት አንድ የሆነ አንድ እግዚአብሔር አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን አምና ታሳምናለች፤ ተምራ ታስተምራለች፡፡ ስለ እግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት፤ ፈጣሪነትና መጋቢነት... የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባላት ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ መሰረት ከአምስቱ አእማደ ምሥጢር አንደኛውን ክፍል ምሥጢረ ሥላሴን እንመለከታለን፡፡

“በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር”ዮሐ.ወን.1፤1፡፡

በቀሲስ ብርሃኑ ጎበና

በተጥባባተ ሥጋ የማይደረስበት ከሰው አእምሮ በላይ የሆነ ሥጋዊ አእምሮ ተመራምሮ የማይደርስበት ጥልቅ ረቂቅ ሰማያዊ ምሥጢር ነው ነገረ መለኮት፡፡በእርግጠኝነት መናገር የምንችለው ይህን ረቂቅ ምሥጢር ለቅዱስ ዮሐንስ ሥጋና ደም እንዳልገለጠለት መንፈስ እግዚአብሔር እንደገለጠለት ነው፡፡ምክንያቱም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የዓሣ አጥማጅ ልጅ የነበረ አርሱም በአባቱ እግር ተተክቶ በገሊላ ባሀር ዓሣ በማጥመድ ይኖር የነበረ ከመጻህፍት ዓለም የራቀ እንደውም ፊደል ካልቆጠሩ ተርታ የሚመደብ ሰው ነበር እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ“ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደተናገሩ ባዩ ግዜ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ”የሐዋ.ሥራ 4፤13፡፡

 

[ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6]

"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"   (.ሆሴዕ 111 ) 

ከመምህር ዮሐንስ  ለማ

Map of the Journey of the Holy Family in Egyptስዕል፡ እመቤታችን ከተወደደ ልጅዋ ጋር በግብጽ በስደቷ ወቅት የተጓዘችባቸውን መንገዶች የሚያሳይ ካርታ (በትልቁ ለመመልከት ካርታው ላይ ይጫኑ)።

ሐዋርያዊት የሆነች ቅድስት  ቤተ ክርስቲያናችን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ክርስቲያናዊ ትውፊታዋን ጠብቃ፣ መንፈሳዊ አገልግሎቷን በሚገባ አራቅቃ፣ ዘመንን በክፍል በክፍል ቀምራ፤ ከመስከረም ጀምሮ እስከ ጳጉሜን ድረስ ያሉት ሰንበታት የራሳቸው የሆነ ከምሥጢረ ድህነት ጋር የተያያዘ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስያሜ ሰጥታ የሰው ልጆችን ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ለማዳን የተደረገው (የተፈጸመው) አምላካዊ የድኅነት ጉዞ እያዘከረች፣ እያስተማረች... ለዘመናት ቆይታለች፣ አሁንም በማስተማር ላይ ናት ። ለወደፊትም እግዚአብሔር እስከ ፈቀደላት ጊዜ ድረስ ስትመሰክርና ስታስተምር ትኖራለች፡፡  እመቤታችን በትልቅ የምስጋና አገልግሎት ከሚከበሩላት በዓላት መካከል የወርሐ ጽጌ (ዘመነ ጽጌ ) አንዱና በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ልብ ውስጥ ጥልቅ የልቡና ፍቅር ያለው  ይሕ የወርሐ ጽጌ ወቅት  አንዱ ነው ፡፡ በመሆኑም በክፍል አንድ ጽሐፍ   የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስደት በማስመልከት ምክንያተ ስደቷንና ተያያዥ ርዕሶችን ማስነበባችን  ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  በስደቷ ወቅት  ያሳለፈቻቸውን  ውጣ ውረድና ተያያዥ ክስተቶችን  እንዲሁም የጉዞዋን ዋና ዋና መዳረሻዎችን ጭምር ለማስነበብ እንሞክራለን፡፡