[ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6]

"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"   (.ሆሴዕ 111 ) 

ከመምህር ዮሐንስ  ለማ

Map of the Journey of the Holy Family in Egyptስዕል፡ እመቤታችን ከተወደደ ልጅዋ ጋር በግብጽ በስደቷ ወቅት የተጓዘችባቸውን መንገዶች የሚያሳይ ካርታ (በትልቁ ለመመልከት ካርታው ላይ ይጫኑ)።

ሐዋርያዊት የሆነች ቅድስት  ቤተ ክርስቲያናችን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ክርስቲያናዊ ትውፊታዋን ጠብቃ፣ መንፈሳዊ አገልግሎቷን በሚገባ አራቅቃ፣ ዘመንን በክፍል በክፍል ቀምራ፤ ከመስከረም ጀምሮ እስከ ጳጉሜን ድረስ ያሉት ሰንበታት የራሳቸው የሆነ ከምሥጢረ ድህነት ጋር የተያያዘ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስያሜ ሰጥታ የሰው ልጆችን ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ለማዳን የተደረገው (የተፈጸመው) አምላካዊ የድኅነት ጉዞ እያዘከረች፣ እያስተማረች... ለዘመናት ቆይታለች፣ አሁንም በማስተማር ላይ ናት ። ለወደፊትም እግዚአብሔር እስከ ፈቀደላት ጊዜ ድረስ ስትመሰክርና ስታስተምር ትኖራለች፡፡  እመቤታችን በትልቅ የምስጋና አገልግሎት ከሚከበሩላት በዓላት መካከል የወርሐ ጽጌ (ዘመነ ጽጌ ) አንዱና በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ልብ ውስጥ ጥልቅ የልቡና ፍቅር ያለው  ይሕ የወርሐ ጽጌ ወቅት  አንዱ ነው ፡፡ በመሆኑም በክፍል አንድ ጽሐፍ   የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስደት በማስመልከት ምክንያተ ስደቷንና ተያያዥ ርዕሶችን ማስነበባችን  ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  በስደቷ ወቅት  ያሳለፈቻቸውን  ውጣ ውረድና ተያያዥ ክስተቶችን  እንዲሁም የጉዞዋን ዋና ዋና መዳረሻዎችን ጭምር ለማስነበብ እንሞክራለን፡፡

[ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6]

"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት" (.ሆሴዕ 111 )

ከመምህር ዮሐንስ ለማ

holyfamily3በክፍል ሁለት ጽሑፌ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በስደቷ ወቅት ከሕጻኑ ልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በስደት የተጓዘችባቸውን ሀገራት ፣ ያሳለፈቻቸውን ውጣ ውረዶችና ተያያዥ ክስተቶችን እንዲሁም የጉዞዋን ዋና ዋና መዳረሻዎች ጭምር ለማስነበብ መሞከሬ ይታወሳል ፡፡ ዛሬም ከክፍል ሁለት ጽሑፌ በመቀጠል በዛሬው በክፍል ሦስት ቀሩ የምላቸውን የጉዞዋን ዋና ዋና መዳረሻዎች እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለማስነበብ እሞክራለሁ ። መልካም ምንባብ ።

[ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6]

"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"   (.ሆሴዕ 111 ) 

ከመምህር ዮሐንስ  ለማ

flight to egyptእንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተክርስቲያን  ሕግና ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን  እስከ ሕዳር 6 ቀን  ያለው 40 ቀን  የእመቤታችንን እና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታችን ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታችን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡

በችርነትሕ ዓመትን ታቀዳጃለሕ መዝ . 64፡ 11

ከመ/ር ዮሐንስ ለማ
የደብሩ ስብከተ ወንጌል ኃላፊ

adey abebaበተሳሳተ ምኞት የተበላሸውን አስቀድሞትኖሩበት የነበረውን አሮጌውን  ሰውነት  ከእናንተ አርቁ ። ልቡናችሁን በዕውቀት አድሱ ፤ በእውነት፤ በጽድቅና በንጽሕና እግዚአብሔርንለመምሰል የተፈጠረውን አዲሱን ስውነት ልበሱ ‘’ (ኤፌ . 4 . 22-24 ) ።

ስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ዕለት ። ከዚህ ዘመን ፤ ከዚህ ዕለትና ከዚሕ ሰዓት ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር ይክበርይመስገን ።   እንኳን ከ2ዐዐ4 ዓ.ምዘመነ ዮሐንስወደ 2ዐዐ5ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ  ( የዘመን መለወጫ )በዓል በሰላምና  በጤና  ሑላችንንምአደረሰን  አደረሳችሁ ፡፡ ፈጣሪያችን ቸሩ መድኅኔ ዓለም ዘመኑን የሰላም፤ የዕድገት ፤ የጤናና የበልጽግና ዘመን ያድርግልን ። ለሐገራችን ለቤተክርስቲያናችን እንዲሑም ለመላው ዓለም እውነተኛውን ሰላምና ፍቅር ያድለን ፤ ያውርድልን ።