[ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6]
"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት" (ት.ሆሴዕ 11፥1 )
ከመምህር ዮሐንስ ለማ
በክፍል ሁለት ጽሑፌ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በስደቷ ወቅት ከሕጻኑ ልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በስደት የተጓዘችባቸውን ሀገራት ፣ ያሳለፈቻቸውን ውጣ ውረዶችና ተያያዥ ክስተቶችን እንዲሁም የጉዞዋን ዋና ዋና መዳረሻዎች ጭምር ለማስነበብ መሞከሬ ይታወሳል ፡፡ ዛሬም ከክፍል ሁለት ጽሑፌ በመቀጠል በዛሬው በክፍል ሦስት ቀሩ የምላቸውን የጉዞዋን ዋና ዋና መዳረሻዎች እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለማስነበብ እሞክራለሁ ። መልካም ምንባብ ።
[ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6]
"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት" (ት.ሆሴዕ 11፥1 )
ከመምህር ዮሐንስ ለማ
እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕግና ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችንን እና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40ው ቀን የእመቤታችንና የጌታችን ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታችን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡
በችርነትሕ ዓመትን ታቀዳጃለሕ መዝ . 64፡ 11
በተሳሳተ ምኞት የተበላሸውን አስቀድሞትኖሩበት የነበረውን አሮጌውን ሰውነት ከእናንተ አርቁ ። ልቡናችሁን በዕውቀት አድሱ ፤ በእውነት፤ በጽድቅና በንጽሕና እግዚአብሔርንለመምሰል የተፈጠረውን አዲሱን ስውነት ልበሱ ‘’ (ኤፌ . 4 . 22-24 ) ።
ስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ዕለት ። ከዚህ ዘመን ፤ ከዚህ ዕለትና ከዚሕ ሰዓት ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር ይክበርይመስገን ። እንኳን ከ2ዐዐ4 ዓ.ምዘመነ ዮሐንስወደ 2ዐዐ5ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ ( የዘመን መለወጫ )በዓል በሰላምና በጤና ሑላችንንምአደረሰን አደረሳችሁ ፡፡ ፈጣሪያችን ቸሩ መድኅኔ ዓለም ዘመኑን የሰላም፤ የዕድገት ፤ የጤናና የበልጽግና ዘመን ያድርግልን ። ለሐገራችን ለቤተክርስቲያናችን እንዲሑም ለመላው ዓለም እውነተኛውን ሰላምና ፍቅር ያድለን ፤ ያውርድልን ።
ከቄሰ ገበዝ ሰሎሞን አልታየ
የደብሩ ቄሰ ገበዝ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ማር እንደ ወተት የሚጣፍጠውን ትምህርቱን ሲያስተምር በተለያዩ ምክንያቶች (ተአምራትን ለማየት፣ ምግበ ሥጋን ለመመገብ፣ ሐሰት አግኝተው ለመፈተን...) የተሰበሰቡት ከአምስት ገበያ በላይ ሕዝብ መሆናችውን በተመለከተ ጊዜ ከፍ ወዳለ ተራራ ወጥቶ በወርቃማ አምላካዊ አንደበቱ በተራራማ ስብከቱ ካስተማራቸው የመንፈሳዊነት፣ የሐዋርያዊነት፣ የአገልግሎት፣ የምግባርና የትሩፋት ትምህርት አንዱ"ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ" ነው፡፡ ይኸው ትምህርት ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያትና በሐዋርያት እግር ሥር የሚተኩ የቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ ምዕመናንና ምዕመናትን የሕይወት መርህ በማድረግ እስከ መጨረሻ ህቅታ ድረስ አጽንተው እንዲጠብቁት የተሰጠ የምግባርና የትሩፋት (የሥነ ምግባር) አስተምህሮ ነው፡፡